ብዙ ሰው ጤናማና ረዥም ፀጉር ይፈልጋል ነገር ግን እንዴት መንከባከብ እንዳለበት አያውቅም………
በየወሩ ፀጉራችን በአማካኝ 0.5 ኢንች ያድጋል ይሄ ማለት በአመት ስናሰላው 6 ኢንች ይሆናል ማለት ነው
ፀጉራችን እንዲያደርግ ምን ማድረግ አለብን
1, ፀጉራችንን ቶሎ ቶሎ አለመታጠብ ። ፀጉርን ቶሎ ቶሎ መታጠብ ለፀጉር ጥሩ አይደለም በተለይ የተጣራ ውሀ የማንጠቀም ከሆነ ማለት የቧንቧ ውሀ በውስጡ ክሎሪን እና ፍሎራይድ ስላለው ፀጉራችን መንታ እንዲያወጣ በቀላሉ እንዲሰባበር ያደርግዋል።
2,ፀጉራችንን ሁሌ ከታጠብን በኋላ ኮንድሽነር መጠቀም አለብን ።ሻንፖ የተሰራው ፀጉር ለማለስለስ ነው በዋነኝነት በሻንፖ ብቻ ታጥበን የምንወጣ ከሆነ ፀጉራችን እንደንጨት ደርቆ ተሰባብሮ ያልቃል ።
3,የምንገዛውን ሻንፖ መምረጥ አለብን።ይሄ ማለት ሻንፖ ስንገዛ ሰልፌት የሌለው መሆን አለበት ሰልፌት የፕሮቲን ጠር ነው ደግሞ ፀጉራችን የተሰራው ከፕሮቲን በመሆኑ ፀጉራችንን ይጎዳዋል ማለት ነው።
4,ፀጉራችንን በተለያዩ ውህዶች እየቀባን መንከባከብ።ለምሳሌ የአቡካዶ ሊሆን ይችላል ወይም የተለያዩ የቅባት ውህዶች የሚስማማንን በሳምንት አንዴ መጠቀም ይኖርብናል ። ፀጉራችንን ውህድ መቀባት የሚጠቅመን ፀጉራችን ጠንካራ እንዲሆንና በቀላሎ አንዳይሰባበር ነው ይሄ ማለት ከቆዳችን እያደገ ጫፍ የሚሰባበር ከሆነ ምንም ለውጥ አናይም
5,ቶሎ ቶሎ ፀጉራችንን በእሳት አለመሰራት ።እሳት ፀጉርን ይጎዳል በተለይ ቶሎ ቶሎ በሚሆን ጊዜ ;ስለዚህ በተቻለ መጠን እሳት መሰራትን መቀንስ አለብን ከቻልን ደሞ ላልተወሰነ ጊዜ መተው።……….
ለዛሬ ያዘጋጀሁት ይሄንን ይመስላል ዘሚ እባላለሁ ጥያቄ ካላችሁ ፃፍልኝ በሰላም ቆዩልኝ ♥️♥️♥️
ዩትዩብ ቻናሌን ከፈለጋችሁ https://www.youtube.com/channel/UCskWw6S02zG-wXk9srf5rTg